ኮሚሽኑ ከተመድ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በአጋርነትና ትብብር ጉዳዮች ላይ ተወያየ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ የተሐድሶ ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በአጋርነትና ትብብር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የመጀመሪያ ዙር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጀምሮ በአደራጅ ኮሚቴው የተከናወኑ ተቋማዊ አደረጃጀቶች፣ የቀድሞ ተዋጊዎች መረጃ ማሰባሰቢያ ፎርማቶች እና የፕሮጀክት ዝግጅት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
በቀጣይ በአጋርነት ሊሰሩ የሚገባቸው ጉዳዮች ተለይተው የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢፌዴሪ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለሰላም ሚኒስቴር ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 565 /2015 የተቋቋመ ነው።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!