Fana: At a Speed of Life!

ለህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ሁሉም መስሪያ ቤቶች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሁሉም መስሪያ ቤቶች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ተናገሩ።

የክልሉ አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ለሁለት ቀናት ሲያካሂዱት የነበረው የ2015 በጀት ዓመት ያለፉት 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተጠናቋል።

በመድረኩ የ2015 ያለፉት 6 ወራት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷በዚህም በዕቅድ አፈፃፀም ሂደት ላይ ያጋጠሙ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተነስተዋል።

በመልካም አስተዳደር ዘርፍ እንደ ክልል በርካታ ክፍተቶች መኖራቸው እና የፀጥታ መዋቅሩን በማጠናከር ችግሮቹን በፍጥነት መፍታት እንደሚገባ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡፡

የህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ለክልሉ ብሎም ለሀገር ስጋት እየፈጠረ እንደሚገኝ የጠቆመው ሪፖርቱ ፥ ህገወጦችን ተከታትሎ በቁጥር ስር ለማዋል የሚደረገው ጥረት መጠናከር እንዳለበት ተ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ፥ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማጎልበት እያንዳንዱ አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ያላሰለሰ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል ፡፡

በክልሉ ያለውን የማዕድን ሃብት በአግባቡ በማልማት ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ የሚያበረክተውን ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ለማጠናከር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍም የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች መኖራቸውን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ የዘርፉ አመራሮች ትኩረት ሰጥተዉ ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል።

በትምህርት ዘርፍም አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመረዉ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት መናገራቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.