Fana: At a Speed of Life!

የዩኒቨርሲቲ የምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ ነገ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ ነገ የካቲት 03 ቀን 2015 ዓ.ም መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እና በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ ነገ የካቲት3 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 12፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስተካክሉ ቀኑ መራዘሙ ተጠቁሟል፡፡

ተማሪዎች በየትምህርትቤቱ በተወከሉ መምህራን በኩል ምርጫቸውን ማስተካከል እንደሚችሉም ተመላክቷል፡፡

ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደማህበራዊ ሳይንስ ቀይረው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች መቀየር የሚችሉት ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ብቻ መሆኑን አውቀው የምርጫ ማስተካከያቸውን በጥንቃቄ እንዲሞሉ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ተማሪዎች ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ የትምህርት የልህቀት ማዕከል ሆኖ መደራጀቱን ም አስገንዝቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.