Fana: At a Speed of Life!

ከ2015/16 የመኸር እርሻ 2 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2015/16 የመኸር እርሻ 50 ሄክታር መሬት በስንዴ ዘር ለመሸፈን እና 2 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለጸ።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተከናወነው የስንዴ ልማት የተገኘው ውጤት በቀጣይ በስፋት ለመሥራት የሚያነሣሣ መሆኑን ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናግረዋል።

ርዕሰ-መስተዳድሩ በክልሉ በ2015/16 ለሚከናወነው የመኸር ስንዴ ልማት በተዘጋጀው ንቅናቄ ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር አካሂደዋል።

በንቅናቄ ሰነድ ግምገማው ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሣ፣ የክልሉ ብልፅግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ  አካላት ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.