Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ እና ሶሪያ በመሬት መንቀጥቀጥ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ21 ሺህ ባለይ መድረሱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ መድረሱ ተገለፀ፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች አሁንም በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት ፍለጋ እያደረጉ ሲሆን ነገር ግን አደጋው ከተከሰተ አራተኛ ቀን ማስቆጠሩን ተከትሎ ተጎጂዎች በህይወት የመገኘት እድላቸው ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡

በአደጋው ምክንያት መኖሪያ ቤታቸውን ያጡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቱርካውያን አስቸጋሪውን በረዷማ የአየር ንብረት በጊዜያዊ መጠለያ እያሳለፉ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ “የክፍለ ዘመኑ ከፍተኛ አደጋ” ሲሉ ገልፀውታል፡፡

የተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አፋዊ ተቋማት ለአደጋው ፈጣን ምላሽ እየሰጡ ሲሆን የዓለም ባንክ ለቱርክ ለአደጋው መቋቋሚያ የሚሆን 1 ነጥብ 78 ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቷል።

በተመሳሳይ አሜሪካ ለቱርክ እና ለሶሪያ የ85 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ እርዳታ ለመስጠት ቃል መግባቷን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.