Fana: At a Speed of Life!

ከድሬዳዋ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ሁሉም ኃይማኖቶች በሠላም፣ በፍቅር፣ በመከባበር እና በአብሮነት በጋራ የሚኖሩበት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያጋጠመው አለመግባባት በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት የቤተ-ክርስቲያኗን ውስጣዊ አሰራር በተከተለ ሠላማዊ መንገድ እንደሚፈታ የድሬዳዋ አስተዳደር የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ እያበረከተም ይገኛል፡፡

በተጨማሪ የእምነት ተቋማት መጠናከር ለአስተዳደራችንም ሆነ ለሀገር አንድነትና እድገት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን በቤተ-ክርስቲያኒቱ ለአራት ተከታታይ ቀናት በከተማችን የተከሄደውን መንፈሳዊ ጉባኤ እንዲሁም የታወጀው የፆምና ምህላ ሥርዓት በሠላም ተጀምሮ ያለአንዳች ችግር እንዲጠናቀቀቅ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ የተፈጠረውን ችግር ሀሰተኛ መረጃና ውዥንብር በመፍጠርና ህዝቡን ወደ አላስፈላጊ ግጭትና ትርምስ ውስጥ እንዲገባ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ፅንፈኛ የፖለቲካ ኃሎች ተቀናጅተው ኢትዮጵያን በማዳከም ለማፍረስ አደገኛ መልእክቶችን በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም የአስተዳደራችን ነዋሪ የሀገሪቱ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የዜጎችን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ያስተላለፈውን ውሳኔ በማስፈጸም ነዋሪው በአብሮነትና በጠንካራ ተሳትፎ በዘላቂነት ያስቀጠለውን የአስተዳደራችንን ሠላም ዛሬም እንደ ወትሮው ሁሉ ራሱን ከጥፋት ኃይሎች በማራቅ በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ የሠላም ባለቤት በመሆን ኃላፊነቱን ይወጣ ዘንድ የድሬዳዋ አስተዳደር ጥሪ ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም በሁለቱም ወገኖች የካቲተ 5 ቀን የተጠራው ሠላማዊ ሰልፍ በአስተዳደሩ ሠላምና በህዝብ ደህንነት ላይ ችግር የሚፈጥር ስለሆነ በአስተዳደሩ ያልተፈቀደ መሆኑ ታውቆ የህግ የበላይነትን እንደሚረጋግጥ አጥብቀን እያሳወቅን የአስተዳደራችን ነዋሪ በተለይ ወጣቱ አንደ ወትሮው ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ የድሬዳዋ አስተዳደር ጥሪ ያቀርዳል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር

የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ. ም

ድሬዳዋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.