Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በቻይና ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማዕቀቡ የተጣለው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) የስለላ ነው ሲል የጠረጠረውን የቻይና ተንሳፋፊ ፊኛ በሚሳኤል መቶ ከጣለ በኋላ ነው፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከቤጂንግ የደህንነት ፕሮግራም ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው ስድስት ኩባንያዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።

የአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የቻይናን “ወታደራዊ ማሻሻያ ጥረቶች በተለይም ከኤሮስፔስ ፕሮግራሞች ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን” በመደገፍ ተቋማቱ በጥቁር መዝገብ ውስጥ ገብተዋል ብሏል።

ከእነዚህም መካከል ቤጂንግ ለደህንነት እና ለሥለላ የምትጠቀምባቸው መርከቦች፣ ተንሳፋፊ ፊኛዎች እና ተዛማጅ ቁሶች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

አዲሱ ማዕቀብ የተጣለባቸው ኩባንያዎችም የአሜሪካ ቴክኖሎጂዎችን ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል ተብሏል።

ማዕቀቡም የቤጂንግ ናንጂንግ ኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ እና የቻይና ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኮርፖሬሽን 48ኛው የምርምር ተቋምን የሚያካትት መሆኑን የአር ቲ ዘገባ ያመላክታል።

የአሜሪካ የኢንዱስትሪ እና የፀጥታ ንግድ ዋና ፀሐፊ አለን ኢስቴቬዝ ቻይና “የከፍታ ተንሳፋፊ ፊኛዎች መጠቀሟ ሉዓላዊነታችንን የሚጥስ እና የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ማዕቀቡም የዋሺንግተንን ብሄራዊ ደህንነት ለመናድ የሚሹ አካላት “የአሜሪካ ቴክኖሎጂዎችን ከማግኘት የሚያቅብ መሆኑንም ነው የገለጹት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.