Fana: At a Speed of Life!

በነገው ዕለት በከተማችን መንገዶች ለፀጥታ ስራ ሲባል ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኞች ዝግ እንደሚደረጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡

ነገ ዕሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል ከቀናት በኋላ በመዲናችን በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚከናወነው የአጀብ እና የፀጥታ ስራዎች ምክንያት በማድረግ ሁሉም የፀጥታ አካላት የሚሳተፉበት ወታደራዊ የተግባር ልምምድ ስለሚከናወን ለዚሁ ሲባል የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪና ለእግረኞች ዝግ እንደሚሆኑ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

 ከጎተራ መሳለጫ ወይም ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ጎተራ መሳለጫ ጋር
 ከቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሀር የሚወስደው ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መስቀለኛ ላይ
 ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ቡልጋሪያ ማዞሪያ
 ከሳር ቤት በአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ሳር ቤት አደባባይ
 ከካርል አደባባይ በልደታ ፀበል ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት ለሚመጡ ካርል አደባባይ
 ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ
 ከአብነት ወደ ጌጃ ሰፈር አብነት አደባባይ
 ከሞላ ማሩ ወደ አብነት ፖሊስ ጣቢያ ለሚመጡ ሞላማሩ መስቀለኛ
 ከበርበሬ በረንዳ ወደ ቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ
 ከተ/ሃይማኖት ወደ ጎማ ቁጠባ ተ/ሃይማኖት አደባባይ
 ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ዝግ የተደረገ ሲሆን ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡
 ከሽሮ ሜዳ ወደ 6 ኪሎ እና ወደ 4ኪሎ የሚያስኬደው መንገድ ሽሮ ሜዳ ጋር የሚዘጋ ሲሆን ከ4 ኪሎ ወደ ቤተ መንግስት የሚወስደው መንገድ ዝግ ተደርጓል፡፡
 ከቀበና ወደ 4ኪሎ ቀበና አደባባይ
 ከጀርመን አደባባይ እና ከሲግናል አካባቢ ወደ 4 ኪሎ ጥይት ቤት ለሚመጡ ጀርመን አደባባይ
 ከካዛንቺስ መናህሪያ ወደ 4ኪሎ እና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሴቶች አደባባይ
 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር
 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደበባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል መስቀለኛ
 ከቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ ወደ መስቀል ፍላወር ቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ
 ከአፍንጫው በር ወደ 6 ኪሎ አፍንጮ በር
 ከፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው 6 ኪሎ ዝግ ይሆናል፡፡
 ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው መንገድ 6 ኪሎ ቶታል ጋር ዝግ የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም ወደ 4 ኪሎ እና በቅርበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመጡ አቋራጭ መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ለእግረኛ ተጠቃሚዎች መስቀል አደባባይ 4ተኛ ክፍለ ጦር ወይም ጥላሁን አደባባይ ዙርያ፣ ኦሎምፒያ ዙርያ፣ ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከሀራምቤ ወደ መሰቀል አደባባይ፣ ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር በ4 ኪሎ ብሔራዊ ቤተ መንግስትና ወደ ቦሌ እንዲሁም ከቀበና ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ዝግ መሆኑን እንዲያውቁት ፖሊስ አሳስቧል።

ስለሆነም ከለሊቱ 11፡ 00 እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ለተሽከርካሪና ለእግረኞች ዝግ ስለሚደረግ ህብረተሰቡ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀምና ከዛሬ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ማንኛውንም ዓይነት ተሽከርካሪም ለረጅምም ይሁን ለአጭር ጊዜ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.