Fana: At a Speed of Life!

ያለንን እምቅ አቅም በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ችለናል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ በግብርናው ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደተቻለ የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የ2015 ዓ.ም የ6 ወር የስራ ዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ አካሂዷል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት÷ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን እና ለማሳደግ የገጠር ግብርና ፋይናንስን በማሳደግ ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ ተደራሽ ማድረግ ይገባል፡፡
ባለፉት 4 ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል፣ በቀጣይ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ስራዎች በመለየት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባም ዶክተር ግርማ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራን ማስፋፋት፣ የተለያዩ ገበያ ተኮር ሰብሎችን በመለየት በክላስተር ሙሉ ፓኬጅ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉ ነው በሪፖርቱ የተገለጸው፡፡
የመስኖ አቅምን በማጎልበት የግብርናውን ዘርፍ ከዝናብ ጥገኝነት ማላቀቅ፣ የእፅዋት ጥበቃ ስራን በትኩረት መስራት፣ የሰብል ዘር ብዜት ስራን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት የዘር ብዜት ችግርን ለመፍታት አበረታች ስራዎች መሰራታቸውም ተነስቷል፡፡
ዘመናዊ የግብርና ሚካናይዜሽን አገልግሎትን ማስፋፋት፣ ሰፋፊ የእርሻ ልማት ስራን በዘላቂነት መስራት፣ በገጠር የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የወጣቶችን ተሳትፎ በሚፈለገው ደረጃ ማሳደግ እና መሰል ጉዳዮች በትኩረት ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸው በሪፖርቱ መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.