Fana: At a Speed of Life!

በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡
 
በወንዶቹ ምድብ አብዲሳ ቶላ በ2:05:42 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ÷ደሬሳ ገለቴና ሃይማኖት አለው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
 
በወንዶቹ ምድብ ኢትዮጵያዊያኑ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ የ2023ቱን የዱባይ ማራቶን በበላይነት አጠናቀዋል።
 
በተመሳሳይ በሴቶቹ የዱባይ ማራቶን ውድድር ደራ ዲዳ ርቀቱን በ2:21:11 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡
 
ሩቲ አጋና ስራነሽ ይርጋ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
 
በሴቶቹም ምድብ ኢትዮጵያዊያዊያን አትሌቶች እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቃቸውን ከዱባይ ማራቶን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.