Fana: At a Speed of Life!

የገበታ ለሀገር ምዕራፍ ሁለት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገበታ ለሀገር ምዕራፍ ሁለት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተካሂዷል።

የገበታ ለሀገር ምዕራፍ ሁለት የሀብት ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እስካሁን ተደራሽ ያልሆኑ ታላላቅ ሐገራዊ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የገበታ ለሐገር ምዕራፍ ሁለት የሐብት ማሰባሰቢያ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷በጋራ በመስራት እና በመትጋት የጀመርናቸውን ፕሮጀክቶን ጨርሰን-አሻራችን ለሚቀጥለው ትውልድ እናስቀምጣለን ብለዋል፡፡

ገበታ ለሐገር የተባበረ እጃችን የሚገነባው ፕሮጀክት ነው ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ ባለሐብቶችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን÷1 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ቃል መገባቱ ተጠቁሟል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.