Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ማይክሮ ፋይናንስ ወደ ባንክነት ተሸጋገረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ማይክሮ ፋይናንስ ወደ ሸበሌ ባንክነት ተሸጋግሯል፡፡

ማይክሮ ፋይናንስ ተቋሙን ወደ ባንክ የማሳደጊያ መርሃግብሩ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በ2003 የተመሠረተው ብድር እና ቁጠባ ተቋሙ፣ “ሄሎ ካሽ” በተሰኘ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት በሥፋት ይታወቃል።

የሸበሌ ባንክ አሁን ላይ ከግማሽ ቢሊየን ብር ላይ በሆነ ካፒታል ሙሉ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ወደሚያስችለው ደረጃ ከፍ ማለቱ ተገልጿል።

ተቋሙ ከአማራ ብድርና ቁጠባ፣ ከኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም በመቀጠል በአገሪቱ ራሱን ወደ ባንክ ያሳደገ ሶስተኛው ተቋም ሆኗል።
በነስሪ ዩሱፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.