Fana: At a Speed of Life!

የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል -ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በ2014 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ፣ ለሚኒስቴሩ ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከቱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከየካቲት 05 ቀን 2015 እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ተገቢውን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሐ ግብር የሚያሳውቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ተማሪዎቹ ከታች በተገለጹት አማራጮች የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ እንደሚችሉም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም Website: https://result.ethernet.edu.et ፤SMS: 9444፤Telegram bot: @moestudentbot

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላሉ ማንኛውም ጥያቄ፡-result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎችን ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ በአካል እንደማይቀበል ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.