Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት ዕውን አድርገናል-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት ዕውን አድርገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ተገኝተው የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት አስጀምረዋል።

ይህን አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ለህዝባችን የተናገርነውን በተግባር ፈጽመን ዛሬ የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት ዕውን አድርገናል ብለዋል።

እኛ የምናልም፣ ያለምነውን የምንናገር፣ የተናገርነውን ቀን ከሌት የምንሰራ፣ የሰራነውን ደግሞ አጠናቀን የምናሳይ ስለመሆናችንም ማረጋገጫ ነው ሲሉም ነው የገለፁት።

ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ከውጭ የሚገባ ስንዴን አስቀርታ ወደ ውጭ ለመላክ አቅዳ ስትሰራ መቆየቷ ይታወቃል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.