በቀይ ባህር ሲጓዙ የነበሩ 383 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከሞት መታደግ ተቻለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀይ ባህር ወደ የመን ሲጓዙ የነበሩ 383 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከሞት መታደግ መቻሉን በጅቡቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
በጅቡቲ 383 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ጭኖ ወደ የመን በመጓዝ ላይ የነበሩ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ጀልባዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦችለፍርድ መቅረባቸውንም በጅቡቱ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤምባሲው የጅቡቲ የባህር ዳርቻ ጥበቃ ሃይል ፍልሰተኛ ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ ለሚያደርጓቸው ዘመቻዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡