Fana: At a Speed of Life!

ሆቴሎች ለአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው እንግዶችን መቀበል ጀምረዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሆቴሎች ለ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው እንግዶችን መቀበል መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር አስታውቋል፡፡
 
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ አስቴር ሰለሞን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ሆቴሎች ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚመጡ እንግዶችን በጥሩ ሁኔታ ለማስተናገድ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገዋል፡፡
 
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራው ኮሚቴ ሆቴሎች ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶችን በምን መልኩ ማስተናገድ እንዳለባቸው መመሪያ መስጠቱን አንስተዋል፡፡
 
በዚህ መሰረትም ሆቴሎች እንግዶችን ያለምንም የጸጥታ፣ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና ሌሎች አገልግሎቶች ችግር ለማስተናገድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ለዚህም ከፖሊስ ጀምሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነው የማህበሩ ፕሬዚዳንት ያረጋገጡት፡፡
 
ከኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያዎች ጋር በተያያዘም ሁሉም ሆቴሎች አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
ከጸጥታ እና ሌሎች ችግሮች ጋር በተያያዘ ችግር ቢያጋጥም ለሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት ለማሳወቅ አጫጭር የሥልክ ቁጥሮች መዘጋጀታቸውንም አስረድተዋል፡፡
 
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.