Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት በ5 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የእህል ግዥ እየተፈጸመ ነው – ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ሕብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን ገበያን ለማረጋጋት በ5 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ ከአርሶ አደሩ የእህል ግዥ እየፈጸመ መሆኑን አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የግብይት ትስስር ባለሙያ አቶ ፋንታሁን ወርቅዬ እንዳሉት÷ ግዥው በ1 ሺህ 650 መሰረታዊ ሕብረት ስራ ማህበራት እና በ23 ዩኒየኖች አማካኝነት ነው እየተከናወነ የሚገኘው።

በተያዘው ዓመት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል እህል ከአርሶ አደሩ በመግዛት ለሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የዋጋ ንረትን ለማርገብ አቅዶ እየሰራ ነው ብለዋል።

ከታህሳስ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ከ176 ሺህ ኩንታል እህል ግዥ መፈጸሙን አቶ ፋንታሁን አብራርተዋል።

ባለስልጣኑ በክልሉ የዋጋ ንረትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቆሎ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ሩዝ እና የመሳሰሉ እህሎችን ከአርሶ አደሩ እየገዛ ለሕብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብ ጠቁመዋል፡፡

በአማራ ክልል 2014 ዓ.ም 166 ሺህ 416 ኩንታል እህል በሕብረት ስራ ማህበራትና በዩኒየኖች አማካኝነት ለሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.