Fana: At a Speed of Life!

በምግብ ራስን ለመቻል የታቀደውን እቅድ እውን ለማድረግ የስንዴ ምርትን በወቅቱ መሰብሰብ ይገባል- አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራስን ለመቻል የታቀደውን እቅድ እውን ለማድረግ የስንዴ ምርትን በወቅቱ መሰብሰብ ይገባል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በዱብቲ ወረዳ እየተከናወነ የሚገኘውን የሥንዴ ምርትን በኮምባይነር የመሰብሰብ ሒደት ጎብኝተዋል፡፡

አቶ አወል በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷በአፋር ክልል የስንዴ ምርትን በስፋት ለማምረት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራስን ለመቻል የታቀደውን እቅድ እውን ለማድረግም የተገኘውን የሥንዴ ምርት ያለምንም ብክነት በወቅቱ መሰብሰብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የአፋር ክልል የሠው ዘር መገኛ መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ስንዴን ከውጭ ከማስገባት ይልቅ በአፋር እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ማምረት እንችላለል ብለዋል፡፡

የአፋር ሕዝብም የስንዴ ምርትን ለማሳደግ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ስኬት ለማስመዝገብ በቅንጅት መስራት አለበት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.