Fana: At a Speed of Life!

የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመማር ያመለከቱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል፡፡

ስለሆነም ተማሪዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

Website: https://placement.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

በሌላ በኩል የ Remedial ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ በነገው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.