Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት በፍጥነት ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በግጭት ሳቢያ ተዘግተው የቆዩ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ስራ ለማስጀመር በትብብት እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ሕዝቅኤል እንደገለጹት÷የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶችን ዳግም ስራ ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
 
የሰላም ስምነቱን ተከትሎም በክልሉ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሁን ላይ ያሉበትን ሁኔታ ለማጥናት የተላከው የሚኒስቴሩ የባለሙያዎች ልዑክ አስፈላጊ መረጃዎችን ሰብስቦ መመለሱን አንስተዋል፡፡
 
በመቀጠልም የሚኒስቴሩ የአመራሮች ቡድን ወደ ክልሉ በመሄድ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ስራ ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መምከሩን ተናግረዋል፡፡
 
በተለይም ትምህርት ለማስጀመር ባሉ አስቻይ ሁኔታዎችና ትምህርት ቤቶቹ አሁንላይ ባሉበት ቁመና ዙሪያ ከየዞኖቹ የትምህርት ስራ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
 
በክልሉ ተቋርጦ የቆየውን የትምህርት አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር የጋር እቅድ በማዘጋጅ በትብብር እየተሰራ መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.