Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን በታርጫ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በመክፈቻው ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ÷ በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል።

በተግባር አፈጻጸም ሂደት መሠረታዊ ለውጦች መኖራቸውን ጠቅሰው÷ትግል የሚጠይቁ ተግባራት እንዳሉ እና ሌብነት ላይ የተጠናከረ የጋራ ትግል ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የግብርና፣ የጤና፣ የትምህርትና የስራ ዕድል ፈጠራ እና የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ጠንካራ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ መቆም ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የክልሉ የስድስት ወራት አፈጸጸም ሪፖርት እየቀረበ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.