Fana: At a Speed of Life!

በሥድሥት ወሩ ለመሰብሰብ ከታቀደው 80 በመቶ ያህሉ ምርት ተሰብስቧል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርት ዘመኑ ለመሰብሰብ ከታቀደው 13 ነጥብ 95 ሚሊየን ሔክታር ውስጥ 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ የሥድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡

በሪፖርቱ ላይ እንደተመላከተው የመስኖ ስንዴ ልማትን በተመለከተ÷ 1 ነጥብ 32 ሚሊየን ሔክታር ለማረስ ታቅዶ እስከ ታኅሣሥ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ 1 ነጥብ 36 ሚሊየን ሔክታር ታርሷል፡፡

ከዚህ ውስጥም 1 ነጥብ 24 ሚሊየን ሔክታሩ በዘር መሸፈኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ከ2014/15 የመኸር ወቅት የአነስተኛ አርሶ አደሮች ሰብል ልማት አኳያ፥ 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር ለማልማት ታቅዶ 14 ሚሊየን ሔክታር በዘር ተሸፍኗል ተብሏል፡፡

ከዚህ ውስጥ የአነስተኛ አርሶ አደሮች የአዝርዕት ሰብል 13 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታር ለማልት ታቅዶ 13 ነጥብ 38 ሚሊየን ሔክታር በዘር መሸፈኑን አመላክቷል፡፡

ከታረሰው መሬት ውስጥ በዘመናዊ የእርሻ ትራክተር የታረሰው 19 ነጥብ 14 በመቶ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በዘር ከተሸፈነው ጠቅላላ መሬት በኩታ ገጠም የታረሰው ደግሞ 45 በመቶ የሚሸፍን ነው ተብሏል፡፡

የአፈር ማዳበሪያ 1 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ለማቅረብ ታቅዶ 1 ነጥብ 17 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን መቅረቡ ተጠቁሟል፡፡

የምርጥ ዘር አቅርቦትን በተመለከተም 75 ሺህ ኩንታል ለማቅረብ ታቅዶ 122 ሺህ ኩንታል መቅረቡን ሚኒስቴሩ ባቀረበው የሥድስት ወር ሥራ አፈጻጸም ላይ ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.