Fana: At a Speed of Life!

በሥድሥት ወራት በጥበባት ዘርፍ ከ68 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት አመቱ በጥበባት ዘርፍ በስድስት ወራት ውስጥ 68 ሚሊየን 583 ሺህ 998 ብር ገቢ መሰብሰቡን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ በሥድሥት ወራት በጥበባት ዘርፍ 90 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ፥ 68 ሚሊየን 583 ሺህ 998 ብር ገቢ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም 4 ሚሊየን 485 ሺህ 667 ግለሰቦች የኪነጥበብ አገልግሎት እንዳገኙና 21 ሺህ 433 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ደግሞ ሕጋዊ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲኖራቸው መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

3 ሺህ 920 ባለሀብቶች በስፖርት ዘርፍ ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስጠቱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በክልሎች እየተገነቡ ያሉ ስታዲየሞች ዓለም አቀፍ ደረጃን ጠብቀው እንዲገነቡ ድጋፍ ማድረግ፣ የቤተ መፃሕፍትን አገልግሎት ለማዘመን የሚያስችል ምክረ ሀሳብ ማቅረብ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል፡፡

በቋንቋ ፖለሲ የተመለከተ ስትራቴጂካዊ ተግባራትን በተደራጀ ሁኔታ ለማከናወን የሚያስችል ተቋማዊ አቅም እና ቅንጅት መፍጠር እንዲሁም የጥበብ ዘርፍ በኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ በመተንተን ድጋፍ ማድረግም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

 

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.