Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ስድስት ወራት የባህር ወደቦችን በመጠቀም ከ518 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ማዳን ተችሏል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት የባህር ወደቦችን በመጠቀም ከ518 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማዳን መቻሉን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባቀረበው የ2015 ዓ.ም የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደገለጸው÷ በኢኮኖሚ አዋጭነት ላይ በመመስረት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ አራት የባህር ወደቦችን ማለትም ጅቡቲ፣ ታጁራ፣ በርበራና ሞያሌ/ሞምባሳን እየተጠቀመች ትገኛለች፡፡

በ6 ወራት ውስጥ ወደቦቹ ያስተናገዱት የጭነት ድርሻ፡-ጅቡቲ 94 ነጥብ 35 በመቶ ፣ ታጁራ 1 ነጥብ 56 በመቶ ፣በርበራ 3 ነጥብ 33 በመቶ ፣ ሞያሌ/ሞምባሳ 0 ነጥብ 76 በመቶ መሆኑን በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

151 ሺህ 551 ቶን ጭነት በታጁራ ወደብ በኩል በመስተናገዱ ለጅቡቲ ወደብ ይወጣ የነበረን 36 ሚሊየን 568 ሺህ 211 ብር የሎጂስቲክስ ወጪን ማዳን መቻሉም ተጠቅሷል፡፡

በአጠቃላይ በሀገር ውስጥ በተለያዩ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ጉዳዮች በተደረገ ጥረት በድምሩ እስከ 518 ሚሊየን 857 ሺህ 513 ነጥብ 4 ብር ወጪን ማዳን መቻሉም ተገልጿል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.