Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ዓመቱ በገቢ ማሳደግ እና የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ አበረታች ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በስድስት ወሩ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን ማሻሻል፣ በገቢን ዕድገት እና በመንገድ ግንባታ ላይ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ ባቀረበው የግማሽ ዓመት ሪፖርት እንደተገለጸው÷ በሰባት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ደረጃዎች ዙሪያ የማሻሻያ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
ከማዘጋጃ ቤት ገቢ አኳያ ዘጠኝ ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 10 ነጥብ 05 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ከመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ አንጻር 164 ሺህ 508 ኪሎ ሜትር ግንባታ ለማከናወን መታቀዱ እና 164 ሺህ 318 ኪሎ ሜትር መከናወኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
በተጠና መልኩ ያልተማከለ የፊሲካል ሥርዓት በማጎልበትም ከተማ አስተዳደሮች ያላቸውን የገቢ አቅም ስራ ላይ ማዋልና የአገልግሎት ክፍያ ወቅታዊ በማድረግ የከተሞችን ገቢ የማሻሻል ሥራ ተሠርቷል ነው የተባለው፡፡
ቆጥበው እና እየቆጠቡ የሚገኙ የ20/80 እና የ10/90 ቤት ተመዝጋቢዎች ዘላቂ መፍትሔ መስጠት የሚቻልባቸውን አማራጮች ለመንግስት በማቅረብ÷ አካታች እና አቅምን ያገናዘበ የቤቶች አቅርቦት አማራጮች እንዲሰፉ ሥራዎች መከናወናቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
ሕገ ወጥ መሬት ወረራ እና ብልሹ አሠራር ለመከላከል ካዳስተር በአስገዳጅነት ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግ አሠራር መዘርጋቱ ተጠቅሷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.