Fana: At a Speed of Life!

በአፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከካናዳ አቻው ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የተመራ የልዑካን ቡድን ከካናዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የልምድ ልውውጥና የሥራ ጉብኝት አካሂዷል፡፡
 
በጉብኝቱ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባዔ ሎሚ በዶን ጨምሮ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
 
ልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከካናዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔና ምክትል አፈ-ጉባዔ፣ ከሴኔቱ አፈ-ጉባዔ፣ ከመንግስት ዋና ተጠሪ ኃላፊዎችና ከሌሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ አባላት ከካናዳ ምክር ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ምሁራን ጋር ባደረጉት ውይይት ሀገሪቱ ከምትታወቅበት የብዝኃነት አያያዝ ልምድ ጠቃሚ ተሞክሮ ማግኘታቸው ተጠቀሟል፡፡
 
በልምድ ልውውጡ ህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝምን ተግባራዊ ለማድረግ እና የሁለቱ ሀገራት ትብብርና ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር መደረጉን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ አባላት ጋር በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች መምከሩም ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.