Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ42ኛውአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

በናይጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆፍሪ ኦኒያማ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ሲገባ በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በተመሳሰይ የኮቲዲቯር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃሚላ ሴኔቪራ በየአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡

ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ  አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 42ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ እንግዶች አዲስ አበባ ከተማ መግባት ጀምረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.