Fana: At a Speed of Life!

በመኖሪያ ቤት አቅርቦትና የከተማ መሬት አስተዳደር ሥርዓት ላይ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግማሽ ዓመቱ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እና የከተማ መሬት አስተዳደር ሥርዓት ላይ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በመንግስት፣ ሪል-ስቴት፣ በግል እና በማኅበራት 119 ሺህ 126 አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ታቅዶ÷ 88 ሺህ 562 ቤቶችን መገንባት መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

50 ሺህ ደረጃቸውን የጠበቁ የገጠር መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን እና 69 ሺህ 817 መገንባቱን የሚኒስቴሩ የሥድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አመላክቷል፡፡

ለተለያየ አገልግሎት የሚውል 5 ነጥብ 6 ሺህ ሔክታር የለማ መሬት በማዘጋጀት ለማስተላለፍ ታቅዶ÷ 4 ነጥብ 9 ሺህ ሔክታር ማከናወን ተችሏል፡፡

6 ሺህ 146 ሔክታር ይዞታዎችን ከሕገ ወጥ ወረራ ነፃ ማድረግ መቻሉ እና 10 ሺህ ሠነድ አልባ ይዞታዎችን ለመለየት ታቅዶ 10 ሺህ 4 የሆኑ ይዞታዎችን መለየት መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡

172 ሺህ 173 ሔክታር መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና ካዳስተር ሽፋን ለመስጠት ታቅዶ ለ109 ሺህ 844 ሽፋን ተሰጥቷል ነው የተባለው፡፡

5 ሺህ 600 ሔክታር መሬት በምደባ እና በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለማድረስ መታቀዱ እና ከ4 ሺህ 923 ሔክታር በላይ መሬት እንዲቀርብ መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.