Fana: At a Speed of Life!

የጅቡቲ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች  ገብተው መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ፡፡

በጅቡቲ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሱፍ ሙሳ ዳዋሌህ የተመራ ልዑካን ቡድን የቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝቷል።

በጉብኝታቸውም የተከናወኑ የልማት ስራዎችንና የባለሀብቶችን እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

ለልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስራ እድል ፈጠራ፣ የኢንቨትመንት አማራጭ እና ለባለሀብቶች ስለሚደረጉ ማበረታቻዎች፣ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በተሰሩ ስራዎች ላይ ገለፃ ተደርጓል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን እንዳሉት÷ጉብኝቱ ከጅቡቲ በቅርብ ርቀት በተገነባው የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የሀገሪቱ ባለሀብቶች ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያነቃቃ ነው ፡፡

የጅቡቲ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሱፍ ሙሳ ዳዋሌህ በበኩላቸው÷ የጅቡቲ ባለሀብቶች በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ገብተው እንዲሰሩ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.