Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት በደረሰ የእሳት አደጋ በስድስት የንግድ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከቀኑ 8:05 ሰዓት ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ንግድ ቤቶች መካከል ÷ የመድኃኒት መሸጫ ሱቆች እና ስጋ ቤቶች ይገኙበታል ብለዋል፡፡

በአደጋው የደረሰው የንብረት ውድመትና የአደጋ መንስኤ እየተጣራ መሆኑን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ምክንያት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም አረጋግጠዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.