Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን የሁለትዮሽ ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን የሁለትዮሽ ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ ኢትዮጵያ በምታደርገው የወጪ ንግድ ገዢነት ስሟ በቀዳሚነት ከሚነሳው ከፓኪስታን ጋር የሁለትዮሽ ንግድ ስምምነት መፈረሙን አስታውቀዋል።

ስምምነቱ የወጪ ንግድ ገቢ ግኝትን በእጅጉ እንደሚያሳድግ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

አያይዘውም ከሌሎች ሀገራት ጋር የተጀመሩ የሁለትዮሽ ንግድ ስምምነት ድርድሮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.