Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ሥራ እንዲጠናከር የባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የባለድርሻ አካላትን የጋራ ጥረት ማጎልበት እንደሚገባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ ።

በአስፈጻሚ ተቋማት የ2015 አፈጻጸም ላይ በተነሱ አስተያየቶች እና የግልጽነት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት ምላሽ፥ በክልሉ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ቅንጅታዊ አሠራሮችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

በትምህርት ሥራዎች ያሉ ችግሮችን በመፍታት ውጤት ለማስመዝገብ ከራስ የጀመረ ለውጥ ማድረግ እንደሚጠበቅም ነው የገለጹት፡፡

ከመንገድ ፕሮጀክቶች አንጻር ያለውን ውስንነት በመለየት የክልሉ መንግስት በትኩረት ይሠራል ተብሏል፡፡

የክልሉ አስፈጻሚ ተቋማት የ2015 የ 6 ወራት የተግባር አፈጻጸም በምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምጽ መጽደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

በክልሉ በግብርና ሥራዎች መሠረታዊ ለውጦች መገኘታቸውንና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እንዲሠሩ ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡

በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ሕገ ወጥ ሥራዎችን ለመከላል በትኩረት እንደሚሠራም ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.