Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ የአገራቱ የመከላከያ ሚኒስትሮች ገለፁ።

የሁለቱ አገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ በተካሄደው 31ኛው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የመከላከያና ጸጥታ ሚኒስትሮች ኮሚቴ ስብሰባ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።

በውይይታቸው÷ ሁለቱ አገሮች በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን በማጠናከር በሁለትዮሽ እንዲሁም በቀጣናው መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ÷ ኢትዮጵያ ከኡጋንዳ ጋር በመከላከያ ዘርፍ በትብብር የሚሰሩበት ሥምምነት አለ ብለዋል።

ሁለቱ አገራት ያደረጉትን ሥምምነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መግባባታቸውንና አጠቃላይ ወታደራዊ ትብብርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

የኡጋንዳ መከላከያ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪሲንቲ ሴቢቻ በበኩላቸው÷ ኡጋንዳ በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር ትፈልጋለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሁለቱ አገራት ቀደም ሲል የነበራቸውን የመከላከያ ሥምምነት ትብብር ማየትና መከለስ የውይይታቸው አንደኛው ጉዳይ እንደነበር ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.