Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና የ1 ነጥብ 22 ቢሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራራሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና የ1 ነጥብ 22 ቢሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የገንዘብ ድጋፉ ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚውል ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ድርጅትን የገንዘብ ችግር በማቃለል ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላልም ተብሏል፡፡
የድጋፍ ስምምነቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ መንግስታት መካከል ከሁለት ዓመት በፊት በተፈረመው የኢኮኖሚ እና የቴክኒክ ትብብር ስምምነት መሰረት የተከናወነ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና የቻይናን መንግስት በመወከል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩሀን ፈርመውታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.