Fana: At a Speed of Life!

የሸገር ባስ አውቶብሶች ለመምህራንና ትምህርት አመራሮች አገልግሎት እንዲሰጡ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሸገር ባስ አውቶብሶች ለመምህራንና ትምህርት አመራሮች አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ፣ የአስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ፣ የከተማው አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው አለሙ፣ የአስተዳደሩ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሌሎች አመራሮች ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ከተማ አስተዳደሩ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ላይ የሚገኙ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሸገር ባስን አሁን እየተጠቀሙበት ባለው መታወቂያ መጠቀም እንዲችሉ መወሰኑ ታውቋል፡፡

በተጨማሪም ሌሎች ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ ከመምህራን የቀረቡ ጥያቄዎችን በተመለከተ በመድረኩ ላይ ውይይት እንድተደረገበት የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይ ችግሮችን በጥናት ለመፍታት እንዲቻል አጥኚ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱም ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.