Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የአመራር ልኅቀት አካዳሚ የመጀመሪያውን የፓን አፍሪካኒዝም ፎረም ሊያካሂድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የአመራር ልኅቀት አካዳሚ የመጀመሪያውን የፓን አፍሪካኒዝም ፎረም የፊታችን ዕሁድ ሊያካሂድ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አካዳሚው ፎረሙን የሚያካሂደው ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው ማሠልጠኛ ማዕከል ነው ተብሏል።

በፎረሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሀገራት መሪዎች እና ቀዳማዊ እመቤቶች እንደሚታደሙበት ተገልጿል።

ታዋቂ ምሁራን በፎረሙ ላይ ፅሁፋቸውን ያቀርባሉም ተብሏል።

ፎረሙ ኢትዮጵያ በ”አረንጓዴ ዐሻራ” ያመጣቻቸው ውጤቶች እንደሚቀርቡበትም አካዳሚው በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተነስቷል።

አካዳሚው ፎረሙን ማካሄዱ አፍሪካ ጠንካራ ልጆችና መሪዎች እንዳሏት ማሳያ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

መድረኩን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ የ“ፓን አፍሪካኒዝም” አስተሳሰብን ለማነቃቃት ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ተነግሯል።

ፎረሙ ላይ 300 እንግዶች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ፎረሙ በየዓመቱ እንደሚካሄድና በመድረኩ የሚነሱ ሐሳቦችም ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችሉ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን እንደሚከናወን ተመላክቷል።

በፍቅርተ ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.