Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት መሩ የሰላም ሂደት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርሕ ያረጋገጠ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት መሩ የሰላም ሂደት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርሕ ያረጋገጠ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
 
በ42ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ደመቀ÷ የሰላም ሒደቱ በትክክለኛ መስመር ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
 
በሰላም ድርድር ሒደቱ ላይ ለተሳተፉ ሁሉም አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
አሁን የተገኙት የሰላም ትሩፋቶች ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን አህጉር በቀል መርሕ በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነም ነው የገለጹት።
 
ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነቱ ምንም ሳይሸራረፍ ተፈጻሚ እንዲሆን ጥረቷን አጠናክራ ቀጥላለችም ነው ያሉት አቶ ደመቀ፡፡
 
በግጭቱ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊው የሰብዓዊ እርዳታ በተፋጠነ መልኩ እየደረሰ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
 
ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ በነበረችበት ወቅት ከአፍሪካ ሀገራት ተገቢውን ድጋፍ ማግኘቷንና ይህም የፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ በተሟላ መልኩ ለቀጣይ ትውልድ መተላለፍ እንደሚችል ያመላከተ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
 
በወንደሰን አረጋኸኝ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.