Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከተሰማሩ ኤጀንሲዎች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ ከተሰማሩ ኤጀንሲዎች ጋር ውይይት እካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ የውጭ ሀገራት ሥራ ስምሪት ዘርፍ ትልቅ ተልዕኮ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ውድድሩ ዓለም አቀፋዊ  በመሆኑ ይህንን ለመወጣት ነባራዊ ሁኔታውን መረዳት ያስፈልጋል ነው ያሉት ሚኒስትሯ፡፡

ውይይቱ ኃላፊነትን ለመወጣት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት በዘመናዊ አሰራር ወደፊት መራመድ የሚቻልበትን ሁኔታ በተመለከተ ሀሳብ የሚነሳበት እና የአቅም ውስንነቶች ካሉ መፍትሔ የሚቀመጥበት መሆኑን ተናግረዋል።

ሀገርን በመገንባት ሒደት የመዋቅር እና የአስተሳሰብ ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን ነው ወይዘሮ ሙፈሪሃት የገለጹት፡፡

የሀገር ሁለንተናዊ ለውጥ ለሥራቸው ስኬታማነት ያለውን ድርሻ መገንዘብ እንደሚገባ መግለጻቸውንም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከ400 በላይ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ የተሰማሩ ኤጀንሲዎች በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተግባራዊ በሚደረግበት የዲጂታል ሲስተም ላይ ስልጠና እንደሚወስዱ ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.