Fana: At a Speed of Life!

ጭፍራ፣ አውራና እዋ ወረዳዎች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በከልዋን ዞን የሚገኙት ጭፍራ፣ እዋና አውራ ወረዳዎችና አካባቢዎቻቸው ዳግም የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
 
የወልድያ ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በመዘረፉ ምክንያት ለረጅም ጊዜ አገልግሎቱ ተቋርጦባቸው የቆዩት እነዚህ አካባቢዎች ከትላንት ጀምሮ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎቹ በአሁኑ ወቅት ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑት የወልዲያ ዶሮ ግብር ባለ 230/33/15 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ነው ተብሏል፡፡
 
በተመሳሳ ሁኔታ ከመኾኒ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ኤሌክትሪክ የሚያገኙ ዳሎል፣ መጋሌ እና ኢሬብቲ ሳተላይት ጣቢያዎች የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎትለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.