Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ኢኮኖሚው እንዲያገግም እና ንግድ ለማሳለጥ ያግዛል – አንቶኒዮ ፔድሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የአውሮፓ ኅብረት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ፔድሮ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና አኅጉራዊ ኢኮኖሚው እንዲያገግም ለማነቃቃት፣ ንግድ ለማሳለጥ ፣ ኢንዱስትሪ ለማስፋት እንዲሁም አቅም ለማጠናከር ጉልበት ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ፡፡

በ42ኛው የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ጉባዔ ላይ በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ፔድሮ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

በያዝነው ዓመት እና በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2024 አፍሪካ ከሌላው ክፍለ ዓለም በበለጠ መልኩ 3 ነጥብ 9 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማስመዝገብ አንፀባራቂ ብርሃን ሆና ትታያለችም ብለዋል።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና አኅጉራዊውን ገበያ ከውጭ የአቅርቦት ሠንሠለት ጋር በማስተሳሰር አኅጉር ተሻጋሪ ንግድ ለማካሄድ መደላድል ይፈጥራልም ነው ያሉት በንግግራቸው።

በማምረቻው ዘርፍ መዋዕለ-ንዋይ የሚያፈሱ ባለሐብቶችን በመጋበዝ እንደ መድሐኒት ፣ ምግብ እና የአፈር ማዳበሪያ ያሉ መሠረታዊ አቅርቦቶችን በራሷ የማምረት ዐቅም እንደምታዳብርም ገልጸዋል።

የአፍሪካን አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዕውን ለማድረግ ሥምምነቱን ያላፀደቁ 10 የአፍሪካ አባል ሀገራት እንዲያፀድቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዮናታን ዮሴፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.