Fana: At a Speed of Life!

የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጠውን የነፃ ንግድ ቀጣና ለመተግበር ጥረቶች ሊቀጥሉ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካውያንን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጠውን የነፃ ንግድ ቀጣና ለመተግበር የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ ገለጹ፡፡

በአፍሪካ ሕብረት የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድ ኢንዱስትሪና ማዕድን ኮሚሽነር አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ የነፃ ንግድ ቀጣና ፕሮጀክት ስላለበት ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ነፃ የንግድ ቀጣና ከካይሮ እስከ ደቡብ አፍሪካ፤ ከሞሪሺየስ እስከ ኬፕቨርዲ ያለውን ሰፊ ገበያ የሚመለከትና ሚሊየን አፍሪካውያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ማምረቻው ዘርፍ፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠናን ጨምሮ በርካታ ዕድሎችን የያዘ መሆኑንም ተናግረዋል።

1 ሚሊየን ኪሎ ሜትር ራዲየስ በጋራ ማስተሳሰር ለጋራ ልማትና ብልፅግና አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል አፍሪካን በትራንስፖርት ለማስተሳሰር አበረታች ጥረቶች መኖራቸውን ጠቁመው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የነፃ የንግድ ቀጣናው ለፖለቲካዊ አንድነትና ጠንካራ አፍሪካዊ ማንነት መሰረት የሚጥል እንደሆነም ነው የተናገሩት።

አፍሪካ በቂ ገበያና የማምረት አቅም ስላላት ለተግባራዊነቱ የመንግስታትን ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅም አስገንዝበዋል።

የሀገራቱን የንግድ ልውውጥ ከማሳለጥ ባሻገር÷ የውስጥ የምርት አቅምን ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለማጎልበት ብሎም ለሥራ ፈጠራ የነፃ የንግድ ቀጣናው ሁነኛ አቅም ይሆናል ነው ያሉት፡፡

የበለፀገች አፍሪካን እውን ለማድረግ ትክክለኛ ዕቅድ ስለሆነ አፍሪካን ለመቀየር ትልቁ መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡

ስምምነቱን በፍጥነት በመተግበር ረገድ ሰፊ ሥራ እንደሚጠይቅ ገልጸው÷ ሀገራት ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሥራ የሚገቡበት ነው ሲሉ አመላክተዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ እና ሃብታሙ ተክለሥላሴ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.