Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ነፃ የአይን ህክምና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶርስ ኦፍ ሆፕ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ከእስራኤል ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ ከተባለ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የነፃ የአይን ህክምና እየሰጠ መሆኑ ተገለፀ።
የግብረሰናይ ድርጅቱ ዋና ተጠሪ አቶ ንጉሴ አለሙ የህብረተሰቡን ችግር በመለየት በተለያዩ ጣቢያዎች የነፃ የአይን ህክምና እየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።
ህክምናው የአይን ጠብታና መነፅር ከማዘዝ በተጨማሪ የአይን ሞራ ቀዶ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ጋር በመተባበር እንዲሰራላቸው እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ህክምናው ከዚህ ቀደም ለ14 ጊዜ እንደተካሄደ እና በዚህ ዙርም በአዘዞ ከተማና ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እየተሰጠ እንደሚገኝ ዋና ተጠሪው ገልፀዋል።
በቀጣይ ቀናትም በዳባት፣ በቆላድባና ደልጊ ከተሞች ህክምና እንደሚሰጥ መናገራቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.