Fana: At a Speed of Life!

የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት እና የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ እና የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄሲካ አሉፖ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ በመጭው ቅዳሜና እሁድ እንደሚካሄድ ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.