Fana: At a Speed of Life!

በ55 ሚሊየን ብር የተገነባው የቓሰና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ እና በሰቆጣ ቃልኪዳን ስምምነት ትብብር በ55 ሚሊየን ብር የተገነባው የቓሰና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቋል።

የሰቆጣ ከተማ ከንቲባ አቶ መላሽ ወርቃለም  ÷ፕሮጀክቱ  በሰከንድ 18 ሊትር ውሃ የሚያመነጭ  ሲሆን አሁን ላይ በሰከንድ 13 ነጥብ 5 ሊትር ውሃ  እያመነጨ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የውሃ ፕሮጄክቱ የሰቆጣ ከተማን የውሃ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይታሰባል ያሉት ከንቲባው ይህ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን  ትብብር ላደረጉ  ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ውሃና ኢነርጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ አብርሃም አሰፋ በበኩላቸው ከዚህ በፊት በወር እና በ15 ቀን አንድ ጊዜ ውሃ ይለቀቅ እንደነበር አስታውሰው ከፕሮጄክቱ መጠናቀቅ በኋላ በየአራት ቀኑ  ውሃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንደሚሆን አስረድተዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ማማሩ አያሌውን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.