Fana: At a Speed of Life!

የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደኅና መጡ ማለት እወዳለሁ” ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.