Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በግጭቱ ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 347 ትምህርት ቤቶች ስራ ጀምረዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በግጭት ሳቢያ ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 347 ትምህርት ቤቶች ዳግም ስራ መጀመራቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዳግም ትምህርት መስጠት ከጀመሩት ትምህር ቤቶች ውስጥ 329ኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ፥ 18 የሚሆኑት ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡

በሰሜን ጎንደር ዞን 126 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 5 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ዳግም ትምህርት መስጠት መጀመራቸውን በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ሕዝቅኤል ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን፣ ሃርቡ፣ ላስታ፣ ራያ ቆቦ እና ቆቦ ከተማ 13 የ2ኛ ደረጃ እና 203 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርት መስጠት መጀመራቸውን ስራ አስፈጻሚዋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ በክልሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት የተጠናከረ ትምህርት እንዲሰጡ የማስቻሉ ስራ  ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

 

 

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.