Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ  አዲስ አበባ  እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡

የሊቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱላህ አል-ላፊ በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት  አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እንዲሁም የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሶው ንጌሶ እና የኮትዲቯር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲኤሞኮ ሜይሊየት በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኮትዲቫር ምክትል ፕሬዚዳንትም ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ ተቀብለዋቸዋል።

36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል በመጪው ቅዳሜና እሁድ እንደሚካሄድ ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.