Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ባንክ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ባንኩ ከሀገሪቱ ጋር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ናቸው- ኡስማን ዲዮን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ባንክ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ባንኩ ከሀገሪቱ ጋር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ናቸው ሲሉ በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን ገለጹ፡፡

በባንኩ የኢትዮጵያ፣ኤርትራ፣የደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ዲዮን ÷ በጎንደር ከተማ ተገኝተው በዓለም ባንክ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ አረንጓዴ ልማት፣ በመልሶ ግንባታ፣ በገጠር የንፁህ መጠጥ ውሀ የተከናወኑ ተግባራትንና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በቀጣይም ይህንን በማስቀጠል ሌሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ባንኩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት በጦርነት ላይ ብትቆይም በዓለም ባንክ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች አፈፃፀማቸው ባንኩ ከሀገሪቱ ጋር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ናቸውም ብለዋል፡፡

በከተማ መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የዓለም ባንክ ከፍተኛ ልማት ባለሙያ አቶ ዋና ዋኬ በበኩላቸው÷ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በሚገኙ 14 ከተሞች የጀመረው ፕሮጀክት አሁን ላይ 117 መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም የከተሞችን ቁጥር በመጨመር የስራ ዕድል ፈጠራ ገቢን በማሳደግ ግልፅነት እና ተጠያቂነትን በማዳበር በከተሞች መሰረተ ልማቶች እንዲስፋፉ ይሰራል ብለዋል።

በስንታየሁ አራጌ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.