Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ምርታማነት ለኢኮኖሚ እድገትና ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ወሳኝ ነው – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ምርታማነት ለኢኮኖሚ እድገት፣ ከድህነት ለመላቀቅና ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጋር ተያይዞ በተዘጋጀው “6ኛው በግብርና የተሠማሩ ሴቶችን ማብቃት” በተሰኘው ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ ለየትኛውም ሀገር ኢኮኖሚ የግብርናው ዘርፍ የጀርባ አጥንት ነው፡፡

በአህጉር አፍሪካ ከ75 በመቶ በላይ የሰው ሃይል በግብርና ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን÷ ግማሽ ያህሉ ደግሞ ሴት ገበሬዎች መሆናቸውን ነው ፕሬዚዳንቷ የገለጹት፡፡

የግብርና ምርታማነት ለኢኮኖሚ እድገት፣ ከድህነት ለመላቀቅና ለምግብ ዋስትና ወሳኝ እንደሆነ መናገራቸውንም ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሴቶች የመሬት ይዞታና የፋይናንስ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ÷ የግብርና አቅርቦት ሰንሰለት ለሴቶች የሚመች እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.