Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ኢትዮጵያ የተጎዱ የውሃ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች በግጭት ሳቢያ የተጎዱ የውሃ መሰረት ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በአስቸኳይ እንደሚያስፈልግ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት÷በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በግጭቱ ምክንያት የውሃ አገልሎት ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎችን ዳግም ለማስጀመር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
 
በዚህ መሰረትም በሶስት ክልሎች በአጭር፣ በመካከላኛ እና በረጅም ጊዜ የሚሰሩ የውሃ መሰረት ልማቶች ተለይተው የጥገና ስራ እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የመልሶ ማቋቋም ስራው ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ኢንጂነር ሃብታሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
በእስካሁኑ ሒደትም በሁሉም ክልሎች 4 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ዳግም የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
 
በሰሜን ኢትዮጵያ የውሃ መሰረት ልማቶችን በሙሉ መልሶ በማቋቋም ዳግም ስራ ለማስጀመርም አስቸኳይ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
 
 
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.